አገር አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር ሊካሄድ ነው - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

139

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2015(ኢዜአ)፡- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 'ብሩህ ኢትዮጵያ 2015 አገር አቀፍ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር' ሊያካሂድ ነው።

ብሩህ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድሩን በተመለከተ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን መግለጫ ሰጥተዋል።

ከግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የተውጣጡ 200 ባለልዩ ተሰጦዎች ወደ ቡራዩ ተሰጥዖ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ገብተው በኢንተርፕርነርሺፕ፣ ሃሳብን ወደተግባር መቀየር እና የንግድ አመሰራረትን በተመለከተ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል፡፡

ከ200 ሰልጣኞች መካከል 70 ተወዳዳሪዎች ተለይተው በዳኞች ፊት ውድድር ያካሂዳሉ ብለዋል።

ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ በሚደረገው ውድድር ለ50 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው የስራ መነሻ የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ጠቅሰዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም