የጋምቤላ ክልል እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2015(ኢዜአ)፡- የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ  አውደ ርዕይ እየጎበኙ ነው። 

ከዚህ ጎን ለጎን በሳይንስ ሙዚየሙ የተዘጋጀውን የጋምቤላ ክልል የግብርና ዐውደ ርዕይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሙድ ከፍተዋል። 


 

በክልል ደረጃ በተዘጋጀው የግብርና አውደ ርዕይ ላይ በክልሉ የተመረቱ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋጽኦና ሌሎች የግብርና ዘርፍ ሀብቶች ለዕይታ ቀርበዋል።

ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና ዘርፉን ሊያሳድጉ የሚችሉ ሌሎች የፈጠራ ስራዎችም በአውደ ርዕዩ ተካተዋል።    

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም