የስምጥ ሸለቆ ምዕራፍ 3 ግድብ የግንባታ ጥናት የውል ስምምነት ተፈረመ

397

ሀዋሳ ግንቦት 24/2015 (ኢዜአ)፡- ከ44 እስከለ 50 ሜጋ ዋት በላይ ሀይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል የተባለለት የስምጥ ሸለቆ ምዕራፍ 3 መካከለኛ የሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የጥናትና ዲዛይን ስራ የውል ስምምነት ተፈረመ።

በኦሮሚያ ክልል በቦረና በደቡብ ክልል ደቡብ የኮንሶ ውሃ አጠር አካባቢወች በሰገን ወንዝ ላይ ተንተርሶ የሚገነባው ግድቡ  ሃይል ከማመንጨት ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ አሰሪ መስሪያ ቤት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጥናቱን ከሚያካሂደው ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽንና ቁጥጥር ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በሀዋሳ ስምምነት ተፈራርመዋል።

 በስምምነቱ ላይ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ እንዳሉት ውሃ አጠር በሆነው የቦረናና ኮንሶ አዋሳኝ አከባቢዎች በሚገኝ ተፋሰስ በሰገን ወንዝ ላይ መካከለኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የመገንባት ዕቅድ ተይዟል።

ሀገራችን የኤሌክትሪክ ሃይልን በተለያዩ አማራጮች እያሰፋች ትገኛለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤  ይህም ለታዳጊ ኢኮኖሚያችን የሃይል አቅርቦት አማራጭ ወሳኝ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል።

ግንባታ ለማካሄድ የቅድመ አዋጭነትና አዋጭነት ጥናት ለማካሄድ የውል ስምምነት የተፈረመው የስምጥ ሸለቆ ምዕራፍ 3 መካከለኛ የሃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ከ44 እስከ 50 ሜጋ ዋት በላይ ሃይል ለማመንጨት የታሰበ መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲኖረው ተደርጎ እንዲጠና የታሰበ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ26 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በመስኖ የማልማት አቅም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱን ተከትሎ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ሎጆችና ሌሎች የመዝናኛ አማራጮችም ኮንሶና አከባቢው ላይ የሚታወቀውን የቱሪዝም ፍሰት ይበልጥ በማስፋት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማጠናከር ይረዳል ተብሎ መታሰቡንም አብራርተዋል።

እንደ ሀገር ሃይል ማመንጨትና የአቅርቦት ስራዎች በአብዛኛው በጊቤና አባይ ተፋሰስ ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆኑን  አንስተው በዚህም የተፈጥሮ ሆነ መሰል አደጋዎች ቢከሰት ሊመጣ የሚችለውን ጫና አስቀድሞ ለመከላከል የተፋሰስ አጠቃቀማችንና የሃይል ስብጥር ከፍ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ግንባታው የሚካሄድበት የሰገን ወንዝ ፍሰቱ በሀገር ውስጥ ብቻ በመሆኑ ስራውን ለማከናወን ምቹ አጋጣሚ መሆኑም ተናግረዋል።

ከ60 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚካሄደው የቅድመ አዋጭነትና የአዋጭነት ጥናት በሚቀጥሉት 18 ወራት የሚካሄድ ነው የተባለው።

ጥናቱ እንደተጠናቀቀም ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የግል አልሚዎች ተረክበው ወደ ግንባታ እንዲገቡ እንደሚደረግ ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

ግንባታውን የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽንና ቁጥጥር ስራዎች ኮርፖሬሽን  ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ተሾመ ሲዳላ ግድቡ በሚያርፍበት አከባቢ የሚኖረውን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ላይ ጥናት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በውሉ መሰረት የባለሙያዎች ስብጥርና ልምድ በመጠቀም የቅድመ አዋጭነትና የአዋጭነት ጥናቱን በ18 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በፊርማው ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ በበኩላቸው በክልሉ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰጠው ዕድል አመስግነዋል።

በዛሬው ዕለት የተፈረመው የሃይል ማመንጫ ግንባታ ስራው አካባቢው በስምጥ ሸለቆ ያለና ውሃ አጠር በመሆኑ በተደጋጋሚ የሚከሰትን ድርቅ ከመከላከል አንጻር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው ነው ያሉት።

የጥናት ስራው በተገቢውና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በክልሉ የሚገኙ ባለሙያዎችና ባለ ድርሻ አካላትን በማቀናጀትና ማህበረሰቡን በማሳተፍ ጠንካራ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

 በኦሮሚያ ክልል በቦረና በደቡብ ክልል ደቡብ የኮንሶ ውሃ አጠር አካባቢወች በሰገን ወንዝ ላይ ተንተርሶ የሚገነባው ግድቡ ከ44 እስከ 50 ሜጋ ዋት ሃይል ከማመንጨት ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም