በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

264

አዲስ አበባ ግንቦት 24/2015(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ ሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

አህመድ ሁሴን በ18ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ አርባ ምንጭ ከተማን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር።

ይሁንና የመጀመሪያ አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰአት ላይ የአርባ ምንጭ ከተማው አሸናፊ ፊዳ በራሱ ግብ ላይ ያስቆጠራት ግብ ሲዳማ ቡናን አቻ አድርጋለች።

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በ35 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል።

በአንጻሩ አርባ ምንጭ ከተማ በ30 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ከቀኑ 10 ሰአት ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም