የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከሶማሊያ ብሔራዊ ፖሊስ አዛዥ እና ከጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ጋር ተወያዩ

333

አዲስ አበባ ግንቦት 22/2015 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ሕብረት ድርጅት ፕሬዝዳንት ደመላሽ ገብረሚካኤል ከሶማሊያ ብሔራዊ ፖሊስ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ሱሉብ አህመድ ፊን እና ከጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዑመር ሁሴን ሀሰን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይቱ አገራቱ በሽብርተኝነት እና ሌሎች የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተቀናጀ የሶስትዮሽ ጥምረት ለመከላከል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።


 

በተጨማሪም የሶስቱን አገራት የፖሊስ መኮንኖችን አቅም ማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በመመካከር በቀጣይ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በጅቡቲ ለመፈራረም መስማማታቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም