የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ ግንቦት 21/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክትን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ኮሚሽኑ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም( IFC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ፕሮጀክት ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ዘመናዊ ተደርገው በተገነቡት የተቀናጀ አግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ላይ መሳብ፣ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግን አላማ ማድረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ፕሮጀክቱ ኦሲቢ ግሎባል እና ትሪፕል ላይን ከተሰኙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማትና አካላት ጋር እንደሚተገበር አመልክቷል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ቁልፍ የሚባሉ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች በተለይም በግብርና ማቀነባበሪያው የኢንቨስትመንት ዘርፍ በኢትዮጵያ የሚገኙ እድል እና አማራጮችን ገብተው እንዲመለከቱ የማድረግ እቅድ እንዳለው ተገልጿል።