ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ግንቦት 21/2015 (ኢዜአ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በድጋሚ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ፕሬዝዳንቱ በድጋሚ መመረጣቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል ያለው የቆየ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ትናንት በነበረው ሁለተኛ ዙር ድምጽ አሰጣጥ ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን 52 ነጥብ 14 በመቶ ድምጽ በማግኘት ተፎካካሪያቸውን ከማል ኪሊዳሮግሉ አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም