በጣልያን ግሪፎኒ ሚቲንግ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

401

አዲስ አበባ ግንቦት 20/2015 (ኢዜአ) በጣልያን ግሪፎኒ ሚቲንግ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በ2023 በጣልያን ግሪፎኒ ሚቲንግ የሩጫ ውድድር በ1 ሺህ 500 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በወንዶች በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር አትሌት መልኬነህ አዘዝ አንደኛ ሲሆን አትሌት አሸናፊ ጋዲሳ የሶስተኝነት ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በሴቶች በ1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ አትሌት ቅሳነት አለም ውድድሩን በቀዳሚነት በመግባት አሸንፋለች።

በዚሁ ርቀት አትሌት ትርሃስ ገብረህይወት ሶስተኛ እንዲሁም አትሌት መብሪሂት መኮንን አምስተኛ  ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ውድድርም አትሌት አሊ አብዱልመና በቀዳሚነት ጨርሷል።

በዚሁ ርቀት አትሌት አራረሶ ነጋሳ ደግሞ በአራተኝነት አጠናቋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም