ቀጥታ፡

በጅማ፣ በሮቤና በአዳማ ከተሞች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ጅማ፣ ሮቤ፣ አዳማ ግንቦት 20/2015 (ኢዜአ) ፦ ለየሀገር መከላከያ ሠራዊት ክብርን የሚገልጽና ድጋፍን የሚያጠናክር ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በጅማ፣ በሮቤና በአዳማ ከተሞች እየተካሄደ ነው።

የጅማ፣ የሮቤና የአዳማ ከተሞችና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር የሚገልጽና ድጋፋቸውን የሚያጠናክር ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

የጅማና አካባቢዋ ነዋሪዎችም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚያጠናክር የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በተመሳሳይ ዜና ሮቤና አከባቢዋ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር የሚገልፅ አጋርነት እና ድጋፍ የሚያጠናክርበት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛሉ።

አዳማ ከተማና አካባቢዋ ሰልፈኞች የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገራችን የሉዓላዊነት ምልክት ነው፤ መከላከያ ተቀላቅለን ሀገራችን እንጠብቃለን፤ መከላከያን እናከብራለን፤ እንወደዋለን፤ በሁሉም ነገር ከጎኑ ነን የሚሉ መፈክሮችን እያስተጋቡ ነው።

እንዲሁም የኢትዮጵያዊነት ዓርማ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በመተንኮስ የስልጣን ፍላጎት ማሳካት አይቻልም፤ የህዝቦች አንድነትና ወንድማማችነትን የሚሸረሽሩ ፀንፈኞች በህግ ይጠየቁልን የሚሉ መልዕክቶችንም በማስተላለፍ ላይ ናቸው ።

ሠልፈኞቹ ከህብረ ብሔራዊ ሠራዊታችን ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ክብርና ሞጎስ ህይወቱን ለሰጠን መከላከያ ሰራዊት፤ መከላከያችን የኢትዮጵያ አንድነት ዓርማችን ነው የሚሉ መፈክሮችን አንግበዋል።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም