ሶስተኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የመዝጊያ መርሐ-ግብር በመካሄድ ላይ ነው

374

አዲስ አበባ ግንቦት 18 ቀን  2015 (ኢዜአ) ፡- "ክህሎት ለተወዳዳሪነት" በሚል መሪ ሀሳብ ላለፋት 5 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሶስተኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የመዝጊያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው የውድድር መድረኩ 267 የሚሆኑ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በተለያዩ ዘርፎች የክህሎት ውድድር አካሂደዋል፡፡

በውድድሩም  በቴክኒክና ሙያ ተቋማት አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዞች የተሰሩ ከ103 በላይ  የተለያዩ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ቀርበው ተጎብኝተዋል፡፡ 

 ከ10 ያላነሱ የዘርፉ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮሩ ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ሥራዎች እና የፓናል ውይይቶችም ተካሂደዋል፡፡ 

በተጨማሪም በሞዴል ኢንተርፕራይዞች የተመረቱ ሀገር በቀል ምርቶችም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች ቀርበው ግብይት ተከናውኗል፡፡ 

የተሻለ ውጤት ላመጡ ተወዳዳሪዎች የሽልማትና የእውቅና መርሐግብር እንደሚካሄድም ተገልጿል።

በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም