በኢትዮጵያና በቻይና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ ነው--ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

154

አዲስ አበባ ግንቦት 18/2015(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና በቻይና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ግንኙነት መፍጠርና በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ መጽሃፍት ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቻይና የምርምር ተቋማት ጋር የእውቀት ልውውጥ ማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡


 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለው የአማርኛ ቋንቋ ትብብር የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ጂያ ዌንጂያን (GIA WENGIAN) በበኩላቸው ቋንቋው በቻይና መሰጠቱ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ ለማስተዋወቅ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ሶስት የአማርኛ መመሪያ መጽሃፍት የተመረቁ ሲሆን ቻይናውያን የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎችም ግጥም አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም