ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከተርኪዬ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ግንቦት 16/2015 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከተርኪዬ አምባሳደር ቤርክ ባራን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተርኪዬ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ተመራጭ ባደረጓቸው የኢንቨስትመንት እድልና አማራጮች እንዲሁም የጋራ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዘርፍ የማስተዋወቅ ስራ ላይ ያተኮረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም