ቀጥታ፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የልዑካን ቡድን ቤጂንግ ገባ

አዲስ አበባ ግንቦት 16/2015(ኢዜአ)፡- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የልዑካን ቡድን ዛሬ ቻይና ቤጂንግ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ቤጂንግ ሲደርስ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች፣ በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሲዮን ኃላፊና አባላት እንዲሁም በቻይና በሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት አቀባበል ተደርጎለታል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም