ቀጥታ፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመሰገነ

አዲስ አበባ ግንቦት 15 /2015(ኢዜአ)፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የተለያየ የገንዘብ መጠን ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመሰገነ።

ጽህፈት ቤቱ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ "የገበታ ለትውልድን ጥሪ ተቀብላችሁ ኃላፊነት ስለወሰዳችሁ፤ ለመጪው ትውልድ የምትመጥን ኢትዮጵያን ለመገንባት የድርሻችሁን ስላዋጣችሁ እናመሰግናለን" ብሏል።

በአስራ አምስተኛው ዙር ይፋ ያደረጋቸው ተቋማት ዝርዝር አቢሲኒያ ባንክ ቃል ከገባው 161 ሚሊዮን 700 ሺህ ብር ውስጥ 80 ሚሊዮን 850 ሺህ ብር እንዱሁም ብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ ቃል የገባውን 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ኩባንያ እያንዳንዳቸው ቃል የገቡትን 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም