የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፎረንሲክ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፎረንሲክ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

አዲስ አበባ ግንቦት 15/2015(ኢዜአ)፦የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ የሚገኘውን የፎረንሲክ ኢንስቲትዩት ጎበኙ።
ኢንስቲትዩቱ በውጭ አገራት ሲሰጥ የነበረውን የፎረንሲክ ምርመራ ሥልጠና በአገር ውስጥ መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።
የኢንስቲትዩቱ ግንባታ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እየተከናወነ ሲሆን ከ1 ቢሊየን 282 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበትም ተጠቁሟል።
ኢንስቲትዩቱ በአገሪቷ ዘመናዊ ፖሊስ ለመገንባት የተጀመረውን ጥረት የሚያግዝ ሲሆን በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ሥልጠናውን የሚጀመር መሆኑ ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ ግንባታ እውን ሆኖ ሥራ ሲጀምርም የዲ.ኤን.ኤ ምርመራን ጨምሮ የአሻራ፣ የሰነድ ምርመራና ሌሎችንም የፎረንሲክ ምርመራ ሥልጠናዎች የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።
የግንባታው ሂደት ከተጀመረ ዘጠኝ ወራት ያስቆጠረ ሲሆን አሁን ላይ አፈጻጸሙ 22 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱም ተጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይም ሌሎች የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን በሂደት ላይ መሆኑ ታውቋል።