ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ3ኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መድረክ በይፋ ከፈቱ

298

አዲስ አበባ ግንቦት 14/2015(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ3ኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መድረክ በይፋ ከፍተዋል።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት 'ክህሎት ለተወዳዳሪነት' በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ቀናት የሚቀጥል ነው።

በውድድሩ የፈጠራ ስራዎች ዐውደ ርዕይ፣ፓናል ውይይትና ሌሎች መርሀ-ግብሮች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ውድድሩ ብቃትና ክህሎት ያላቸው ወጣቶች መብቃታቸውን ለማሳየትና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ሁነኛ ሚና ይኖረዋል።

ኢትዮጵያን ለማበልፀግና ሁሉንም ዘርፍ ለማዘመን ፈጠራ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የግብዓት ችግር ባለመኖሩ ፈጠራና ክህሎትን ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያመላከቱት።

የፈጠራ ባለሙያዎች በሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ሳይበገሩ ፈተናዎችን እንደመስፈንጠሪያ ተጠቅመው፤ ውጤት ተኮር ስራዎች ላይ አበክረው እንዲሰሩም አሳስበዋል።

ዛሬ በቀረቡ የፈጠራ ስራዎችም ትልቅ ተስፋ ሰጭ ፈጠራዎችን እንደተመለከቱ ገልፀው፣ ሚኒስቴሩ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ስራዎች ማከናወኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም