የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎበኙ
አዲስ አበባ ግንቦት 14/2015 (ኢዜአ) ፦ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ "ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎበኙ።
በጉብኝቱም ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የአፋር ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል።
ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ በሚል መሪ ሃሳብ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው የግብርና ሳይንስ ኢግዚቢሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተመርቆ መከፈቱ ይታወቃል።
በአውደ ርዕዩ በግብርናው ዘርፍ የተገኙ የተለያዩ ስኬቶችን የሚያሳዩ የተለያዩ የምርምርና የፈጠራ ስራዎች፣ ዲጅታላይዜሽንና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ ቀርበዋል።
አውደ ርዕዩን የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየጎበኙት ይገኛል።
አውደ ርዕዩ በግብርና ሚኒስቴር፣ በግብርና ትራስፎርሜሽን ኢንስቲትዩትና በኢትዮ-ቴሌኮምና ሌሎች አጋር አካላት የተዘጋጀ ነው።