ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቭዥንን በጊዜያዊነት አገደ

አዲስ አበባ ግንቦት 13/2015(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቭዥንን በጊዜያዊነት ማገዱን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው የቴሌቭዥን ጣቢያው ግንቦት 13/2015 ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙሃን ሚና ውጭ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሒደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት አሰራጭቷል ብሏል።

በመሆኑም ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት አንጻር በቀጣይ በባለስልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥብት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት መታገዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታውቋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም