በፕሪሚየር ሊጉ ሀዲያ ሆሳዕና ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ግንቦት 13/2015(ኢዜአ):-በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ የመጀመሪያ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሰመረ ሀፍታይ በ29ኛው እንዲሁም ተመስገን ብርሃኑ በ50ኛው ደቂቃ ለሀዲያ ሆሳዕና የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ናይጄሪያዊው ተከላካይ ቻርለስ ሪባኑ በ69ኛው ደቂቃ ለባህር ዳር ከተማ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ሀዲያ ሆሳዕና በ36 ነጥብ ከ6ኛ ደረጃ ወደ 5ኛ ከፍ ብሏል።

በአንጻሩ ባህር ዳር ከተማ በ50 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ወላይታ ድቻ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ ይጫወታል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ካሸነፈ ከተከታዩ ባህር ዳር ከተማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም