ቀጥታ፡

አገር ለማስቀጠል የሚደረገውን ሂደት በጠንካራ የውይይት ባህል መደገፍ ይገባል - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን

አሶሳ ግንቦት 12/2015 (ኢዜአ) ፡-  አገርን ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው ከሕዝብ ጋር በግልጽና በጠንካራ የውይይት  ባህል  መደገፍ  እንደሚገባ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የቋንቋ መምህር የሆኑት ዶክተር ጌታቸው ወዲሻ እንዳሉት፤ "የኢትዮጵያ እድገት ከጎተቱ ዋነኛ ጉዳዮች አንዱ ግልጸኝነት የተሞላው ውይይት አለመደረጉ ነው፤ውይይት አገርን ይለውጣል ለማህበረሰባችን ጥያቄ መላሽ መስጠት ያስችላል"፡፡

መወያየት ሕብረተሰቡ ጥያቄውን ያለ ስጋት በግልጽነት ለመንግስት ማቅረብ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ለመፍትሄው አብሮ ለመስራት እንደሚያነሳሳው ገልጸዋል፡፡

ይህም በመንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመንን እንደሚያጎለብት አመልክተዋል።

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህርና ዲን ኪዳኔ ደያሳ  በበኩላቸው፤ በዴሞክራሲ ስርዓት ውስጥ ወሳኝ ከሚባሉት አንዱ ግልጽነት መሆኑንና ለዚህ ደግሞ ውይይት ግንባር ቀደም ቦታን እንደሚይዝ  ገልጸዋል።

በሁለንተናዊ አገር ግንባታ ሕዝብን ለማሳተፍ አካታች አካሄድን መተግበር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ የሕብረተብ ክፍሎች ፍላጎታቸውን ለመረዳት ጥልቀት ያለው ውይይት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ልዩነት ለአገር የሚጠቅም ቅርጽ ማስያዝ የሚቻለው በሰከነ መንገድ በመነጋገር ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም