በገበታ ለትውልድ ገቢ ማሰባሰብ ዙሪያ ከሚስዮን መሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በገበታ ለትውልድ ገቢ ማሰባሰብ ዙሪያ ከሚስዮን መሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ ግንቦት 12/2015(ኢዜአ)፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የዲያስፖራ አገልግሎት በገበታ ለትውልድ ገቢ ማሰባሰብ ዙሪያ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሚስዮን መሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ።
በበይነ መረብ የተደረገውን ውይይት የመሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ቡርቱካን አያኖ ናቸው።
በውይይቱም ገበታ ለትውልድን ለመደገፍ በሚስዮኖች እየተከናወኑ ስለሚገኙ ስራዎች እና እየተገኙ ስላሉ ውጤቶች እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከአምባሳደሮች እና ሚስዮን መሪዎች ጋር ምክክር እንደተደረገ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መረጃ ያመለክታል።
ገበታ ለትውልድ በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች የተመረጡ ስምንት የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎችን ለማልማት የተቀረፀ የልማት ኘሮጀክት ነው።