የኢትዮ-የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ፎረም በአቡ ዳቢ ከተማ ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮ-የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ፎረም በአቡ ዳቢ ከተማ ተካሄደ
አዲስ አበባ ግንቦት 11/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮ-የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ፎረም በአቡ ዳቢ ከተማ ተካሄደ።
የቢዝነስ ፎረሙ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን ማስተዋወቅ አላማው ያደረገ እንደሆነም ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በፎረሙ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ለባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች እና ለዘርፉ ምቹነት የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻዎች ላይ ማብራሪያ መስጠታቸው ተመላክቷል፡፡
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን እና ኮሚሽነር ለሊሴ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ዝግጁነትም አስረድተዋል፡፡
ፎረሙ የኢንቨስትመንት ከባቢውን በማነቃቃት እና ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የኢንቨትመንት ግንኙነት በማጠናከር በኩል ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡