ቀጥታ፡

የኮንስትራክሽን ኤክስፖ የንግድ አውደ ርዕይ እና የሚኒስቴሪያል ፎረም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ግንቦት 10/2015(ኢዜአ)፦ የኮንስትራክሽን ኤክስፖ የንግድ አውደ ርዕይ እና የሚኒስቴሪያል ፎረም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ጀመረ፡፡

በኤክስፖው ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ከ26 ሀገራት የተውጣጡ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ተገኝተዋል።


 

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ዮናስ አያሌው ኤክስፖው ለኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እድገት ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ለማግኘት የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተለይም አለም የደረሰበት የግንባታ ቴክኖሎጂን ከኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የንግድ ትርኢቱ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት እና መሰል የኤክስፖ ዝግጅት ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

ከንግድ ትርኢቱ ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት ኩባንያዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም