የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ጁባ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ጁባ ገባ
አዲስ አበባ ግንቦት 9/2015(ኢዜአ) የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።
ልዑኩ ጁባ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ አቀባበል አድርገውለታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ በደቡብ ሱዳን በሚኖረው ቆይታ ኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለመው ላፕሴት ፕሮጀክት አስመልክቶ በተዘጋጀው ውይይት ላይ እንደሚሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
የላፕሴት ፕሮጀክት እ.አ.አ በ2012 በኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳን አገራት መሪዎች የጋራ ስምምነት ወደ ስራ እንዲገባ ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው።