ቀጥታ፡

የአቡዳቢ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በስሩ የሚገኙ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ማበረታቻ እንደሚያደርግ ገለጸ


አዲስ አበባ ግንቦት 9/2015(ኢዜአ):-የአቡዳቢ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በስሩ የሚገኙ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ማበረታቻ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ኡመር ሁሴን ከምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አሊ ቢን ሃርማል ጋር ተወያይተዋል።


 

አምባሳደር ኡመርና ዶክተር አሊ በውይይታቸው ላይ ቀስ በቀስ ለውጥ እያሳየ ስላለው የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር አንስተዋል።

የአቡዳቢ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤትና መንግስት በምክር ቤቱ ስር የሚገኙ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ማበረታቻ ለማድረግ መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እ.አ.አ በ1969 የተቋቋመው የአቡዳቢ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በአቡዳቢ ከተማ የሚገኙ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን ፍላጎት ወክሎ የሚሰራ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም