ቀጥታ፡

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከዱባይ ዓለም አቀፍ ምክር ቤት የመካከለኛው ምስራቅና የአፍሪካ ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ግንቦት 8/2015(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከዱባይ ዓለም አቀፍ ምክር ቤት የመካከለኛው ምስራቅና የአፍሪካ ኃላፊ ካሊድ አል አሊ ጋር በዱባይ ውይይት አድርገዋል።

ምክክሩ ከቀጣናው አዲስ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ መንገዶችና የኢንቨስትመንት አጋርነቶች እንዲሁም የጋራ ፕሮሞሽን ስራዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም