የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያየ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ ግንቦት 08/2015(ኢዜአ)፦ በቻይና ቤጂንግ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የልዑክ ቡድን ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ሀላፊዎች ጋር መክሯል ::
በምክክሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል በ 2022 በተፈረመው እና የሀገራችንን የኢንቨስትመንትና የንግድ አማራጮችን በጋራ ማስተዋወቅን አላማ ባደረገው የመግባቢያ ሰነድ አፈፃፀም ሂደት ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እና የቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጀነራል ሊ ያንግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ወይ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።