ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ ከኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ ከኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ግንቦት 08/2015(ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቤላሩስ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ዲሚትሪ ሉካሼንኮን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
አቶ ደመቀ የክብር ቆንስሉ በቤላሩስ እና በምስራቅ አውሮፓ ኢትዮጵያን በመወከል ላሳዩት ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ቤላሩስ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የሚያጠናክሩበት ጊዜ ነው ያሉት አቶ ደመቀ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በግብርና ሜካናይዜሽን እንዲሁም በማዕድን ዘርፎች የተጀመሩ ትብብሮችን በማጠናከር የኢትዮ-ቤላሩስ ግንኙነትን ይበልጥ ለማጎልበት ይሰራል ብለዋል።
በቤላሩስ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ዲሜትሪ ሉካሼንኮ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
የክብር ቆንስሉ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ስለሚገኘው ልማት እና መልካም ለውጥ ያላቸውን አድናቆትም ገልጸዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል።