ቀጥታ፡

በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ጋር ትውውቅ አደረጉ

አዲስ አበባ ግንቦት 7/2015(ኢዜአ)፦ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባደር እፀገነት በዛብህ በዩጋንዳ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ አባላት ጋር ትውውቅ አደረጉ።


 

በመረሃ-ግብሩ ላይ የተለያዩ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ክፍሎችን የወከሉ እንግዶች የተገኙ ሲሆን አምባሳደሯ ባደረጉት ንግግር ሚሲዮኑ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ጋር በቅርበት ይሰራል ብለዋል።

በኡጋንዳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ አባላት የአገራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም