ፊቼ ጨምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ደረጃ በወዳጅነት አደባባይ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ፊቼ ጨምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ደረጃ በወዳጅነት አደባባይ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ግንቦት 5/2015(ኢዜአ)፦የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ፊቼ ጨምበላላ በወዳጅነት አደባባይ እየተከበረ ነው ።
በበዓሉ አከባበር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመዲናዋ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር ፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።
በዓሉ የሲዳማን ባህላዊ እሴቶችና ማህበራዊ ክዋኔዎች በሚያሳዩ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
የጨምበላላ ዘመን መለወጫ በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች ከተመዘገቡ የኢትዮጵያ በዓላት ውስጥ አንዱ ነው።