ቀጥታ፡

በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሪው ዲከንስ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል--ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ግንቦት 4/2015(ኢዜአ)፦ በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሪው ዲከንስ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ ቀጥታ በረራ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ፣ በረራው የሁለቱን ከተሞች እና የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የሚያጠናክር፤ ወደ ከተማችን የሚመጡ ቱሪስቶችን ቁጥር ከፍ ማድረግ የሚያስችል ስለሆነ በትብብር ለመስራት ተስማምተናል” ብለዋል።

አክለውም “አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ከተሞችን እና ተቋማትን መሳብ የጀመረችና በማበብ ላይ ያለች ታላቅ የዲፕሎማሲና የቢዝነስ ማዕከል እንደመሆኗ፣ የተሻሉ ልምዶችን መካፈል የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር በማድረግ ለከተማችን እድገት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም