የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የአምስት ዓመቱን የለውጥና የስኬት ጉዞ የሚዘክር መርሐ-ግብር እየተከናወነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የአምስት ዓመቱን የለውጥና የስኬት ጉዞ የሚዘክር መርሐ-ግብር እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ ግንቦት 4/2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የአምስት ዓመቱን የለውጥና የስኬት ጉዞ የሚዘክር መርሐ-ግብር እየተከናወነ ነው።
በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ ምክትል ኮሚሽነሮች እና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያን ሰላምና የህዝቦቿን ደህንነት ለማስጠበቅ መስዕዋትነት የከፈሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በመርሃ ግብሩ ይዘከራሉ።
በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን ለማርገብ በጀግንነት ለተፋለሙ ጀግኖችም ዕውቅናና ሽልማት ይሰጣል።
ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስን ጨምሮ በጸጥታ ተቋማት የሪፎርም ስራዎች መሰራታቸው ይታወቃል።
የዛሬው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የአምስት ዓመታት የለውጥና የስኬት ጉዞን የሚዘክረው መርሐ-ግብር የዚሁ ሪፎርም ማሳያ መሆኑ ተጠቁሟል።