በአትላንታ ከንቲባ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በአትላንታ ከንቲባ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ ግንቦት 3/2015 (ኢዜአ) ፦በከንቲባ አንድሬ ዲከንስ የተመራ የአትላንታ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ መግባቱ ተገለጸ።
የልዑክ ቡድኑ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል::
ልዑኩ በአዲስ አበባ ቆይታው ሁለቱ ከተሞች በጋራ በሚሰሩባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
በአትላንታ ከንቲባ የተመራው ልዑክ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኝም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል::