ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በስዋዚላንድ የአፍሪካና የአረቡ አለም ምክር ቤቶች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ ግንቦት 3/2015(ኢዜአ)፦ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ዛህራ ሁመድ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በስዋዚላንድ የአፍሪካና የአረቡ አለም ምክር ቤቶች ጉባዔ (ASSECAA) ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በጉባዔው ላይ የተለያዩ የአፍሪካና የአረቡ አለም አፈ-ጉባዔዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እየተሳተፉ እንደሚገኙም ተገልጿል።

በጉባኤው እያጋጠሙ ያሉ የተለያዩ ቀውሶች በአለማችን፣ በአፍሪካና በአረቡ አለም ኢኮኖሚ ላይ በሚያሳርፉት ተፅዕኖ ላይ ውይይት እንደሚደረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ይጠቁማል።

ከዚህም በተጨማሪ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለዘላቂ ልማት ያለው አስተዋፅኦ ላይ በስፋት የሚወያይ ሲሆን፤ ምክትል አፈ-ጉባዔ ዛህራ ሁመድ በመድረኩ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም