የተርኪዬ ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ሳራር ግሩፕ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስመንት እድሎችን የማየት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የተርኪዬ ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ሳራር ግሩፕ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስመንት እድሎችን የማየት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
አዲስ አበባ ግንቦት 2/2015(ኢዜአ):- የተርኪዬ ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ሳራር ግሩፕ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስመንት እድሎችን የማየት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የልዑካን ቡድን በተርኪዬ ጉብኝት በማድረግ ላይ ነው።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በኤስኪሼሂር ኢንዱስትሪ ዞን ከሚገኙት ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያዎች አንዱ የሆነውን ሳራር ግሩፕን ጎብኝተዋል።
ኩባንያው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ቅርንጫፎችን ከፍቶ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።
ሳራር ግሩፕ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን ይበልጥ የማወቅ ፍላጎት እንዳለውና ለቀጣይ ስራዎች ተርኪዬ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በትብብር እንደሚሰራ አመልክቷል።
በሌላ በኩል ልዑኩ በኤስኪሼሂር ከተማ የሚገኘውን የሰሊጥ ማቀነባበሪያ ኩባንያ አስላን ጎብኝቷል።
ኩባንያው ዘይትና ‘ታሂኒ’ የተሰኘውን ምግብ ለማምረት የሚያስፈልገውን ሰሊጥ ከኢትዮጵያ እንደሚያስመጣ ተገልጿል።
በጉብኝቱ ላይ በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ ተገኝተዋል።