የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተና ቀናትን ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተና ቀናትን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ግንቦት 1/2015(ኢዜአ):- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተና ቀናትን ይፋ አድርጓል።
የትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱንና ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ አሳስበዋል።
በ2015 ዓ.ም 75 ሺህ 100 የ8ኛ እንዲሁም 75 ሺህ 78 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።