ቀጥታ፡

ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል--የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ግንቦት 1/2015(ኢዜአ)፦ ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ከዛሬ ግንቦት 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ በመላ አገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዲጂታል የነዳጅ ግብይቱን አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮ ቴሌኮም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ይህ ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ስርዓት ከዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን በመግለጫው ተነስቷል።

ዲጂታል የነዳጅ ግብይት በዋናነት የመንግሥትን የድጎማ ጫና መቀነስ፣ የህዝብ ትራንስፖርቶች በቂ የነዳጅ ተደራሽነት እንዲኖራቸውና የነዳጅ ሀብት ብክነትን ማስቀረት የግብይቱ ዋነኞቹ ዓላማዎች መሆናቸው ተመላክቷል።


 

ለዚህም እስካሁን በኢትዮ ቴሌኮም በለማው ቴሌ ብር እና በንግድ ባንክ በለማው ሲ ቢ ኢ ብር አማካኝነት ግብይቱ እንደሚፈጸም ተገልጿል።

በአዲስ አበባ የነዳጅ ግብይቱ ላይ ሲከሰት የነበረው ጫናና መጨናነቅ እንዳይከሰት በሙከራ ምእራፍ ላይ በቂ ዝግጅት ሲደረግ እንደነበርም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም