“አዲስ አበባን በአዲስ የዲፕሎማሲ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
“አዲስ አበባን በአዲስ የዲፕሎማሲ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ግንቦት 1/2015(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት እና ኦቪድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመተባበር "አዲስ አበባን በአዲስ የዲፕሎማሲ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም፣ የባሕርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ፣ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ዲፕሎማቶች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።