በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ - ኢዜአ አማርኛ
በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ
አዲስ አበባ ሚያዚያ 30 /2015(ኢዜአ )፡- በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።
ተቋሙ በሕገ መንግስቱ መሰረት የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን በውይይቱ ላይ መገምገሙ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራልና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ሕብረት ፕሬዝዳንት ደመላሽ ገብረሚካኤልና ሌሎች ከፍተኛ የተቋሙ አመራሮች ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።