በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን የሚታደጉ በጎ ፈቃደኞች እና ሠራተኞች ተግባር የተጎጂዎችን ተስፋ የሚያለመልም ሰብዓዊ አገልግሎት ነው … ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ - ኢዜአ አማርኛ
በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን የሚታደጉ በጎ ፈቃደኞች እና ሠራተኞች ተግባር የተጎጂዎችን ተስፋ የሚያለመልም ሰብዓዊ አገልግሎት ነው … ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29/2015(ኢዜአ)፦በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን የሚታደጉ በጎ ፈቃደኞች እና ሠራተኞች ተግባር የተጎጂዎችን ተስፋ የሚያለመልም ሰብዓዊ አገልግሎት መሆኑን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የበላይ ጠባቂ ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ገልጹ፡፡
ቀኑ "ከልብ ለሰብዓዊነት" በሚል መሪ ሀሳብ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ76ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ65ኛ ጊዜ ይከበራል።
ፕሬዚዳንቷ ለአለም አቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።
በመልእክታቸውም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን የሚታደጉ በጎ ፈቃደኞች እና ሠራተኞች ተግባር የተጎጂዎችን ተስፋ የሚያለመልም ሰብዓዊ አገልግሎት መሆኑን ገለጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ላለፉት 87 ዓመታት ሰብዓዊነትን በልባቸው ባነፁ በጎ ፈቃደኞችና ሠራተኞች እየተመራ ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ አንጋፋ ማኅበር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያም በግጭትና ድርቅ አደጋዎች ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን ህይወት ለመታደግ የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኞችና ሠራተኞች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ መንቀሳቀሳቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡
የበጎ ፈቃደኞቹና ሠራተኞቹ ለሰብዓዊ አገልግሎት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የህይወት መስዋዕትነት ጭምር በመክፈል ለሚያደርጉት ወደር የሌለው ሰብዓዊ ተግባር ከፍተኛ አድናቆት እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡
ህብረተሰቡም በሰብዓዊ አገልግሎት ላይ ከተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች ጎን በመቆም ለማህበሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡