ታዋቂው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ - ኢዜአ አማርኛ
ታዋቂው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 27/2015 (ኢዜአ)፦ታዋቂው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
በቅርቡ ለሥራ ወደ ጣሊያን ሀገር የተጓዘው የክላርኔት ተጫዋች ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው በተኛበት ክፍል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን ከቅርብ ወዳጆቹ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዳዊት ፍሬው የክላርኔት የሙዚቃ መሳሪያውን እየተጫወተ የሰራው ሶስት የሙዚቃ አልበም ያለው ሲሆን የአንጋፋው ድምፃዊ ፍሬው ሀይሉ ልጅም ነው፡፡