ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ምዕራፍ ሁለት የስካይ ላይት ሆቴልን መርቀው ከፈቱ


አዲስ አበባ ሚያዝያ 27/2015(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ  ምዕራፍ ሁለት የስካይ ላይት ሆቴልን መርቀው ከፍተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ያስገነባውን ምዕራፍ  ሁለት ስካይ ላይት ሆቴል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት  ዛሬ በይፋ አስመርቋል።

በመረሃ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ዲፕሎማቶች ታድመዋል።

ምዕራፍ ሁለት የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በአፍሪካ ደረጃ እጅግ ዘመናዊ መሆኑ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም