ቀጥታ፡

82ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ሚያዚያ 27/2015(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያውያን አርበኞች የጣልያንን ወራሪ ኃይል ድል ያደረጉበት 82ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል አራት ኪሎ በሚገኘው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ኃውልት በመከበር ላይ ይገኛል።


 

በበዓሉ ላይ አባት አርበኞች፣ እናት አርበኞች፣የአርበኛ ቤተሰቦች፣የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣የአገር መከላከያ ሰራዊት ተወካዮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

በበዓሉ ላይ ለአርበኞች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም