በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ የተመራ ልዑክ የታጁራ ወደብ እና የዳመርጆ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ የተመራ ልዑክ የታጁራ ወደብ እና የዳመርጆ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎበኘ
አዲስ አበባ ሚያዚያ 24/2015(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ የተመራ ልዑክ የታጁራ ወደብ እና የዳመርጆ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎብኝቷል።
ልዑኩ በጅቡቲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
ልዑኩ በታጁራ ወደብና ዳመርጆ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጉብኝት ማድረጉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ገልጿል።
ከዚህ ቀደም ልዑኩ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ፣ የጅቡቲ ነጻ የንግድ ቀጠና፣ የኤስጂቲዲ የኮንቴይነር ተርሚናልና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ስለመጎበኝ መዘገባችን ይታወሳል።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ ከጅቡቲ ወደቦችና ነጻ የንግድ ቀጠና ሊቀ-መንበር አቡበከር ኦማር ሃዲ እና ከዶራሌ ሁለገብ ወደብ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃማ ኢብራሂም ዳራር ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት ኢትዮጵያና ጅቡቲ በሎጅስቲክስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከርን አላማ ያደረገ መሆኑን ኤምባሲው አመልክቷል።