በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23/2015 (ኢዜአ)፦ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስንታየሁ መንግስቱ በ37ኛው እንዲሁም አበባየሁ አጂሶ በ49ኛው ደቂቃ ለወላይታ ድቻ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ነጥቡን ወደ 30 ከፍ ቢያደርግም ተመሳሳይ ነጥብ ባለው ፋሲል ከነማ በግብ ክፍያ ተበልጦ በነበረበት 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በአንጻሩ ለገጣፎ ለገዳዲ በ11 ነጥብ የመጨረሻውን 16ኛ ደረጃ ይዟል።
በ22ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ-ግብር ፋሲል ከነማ ከሀዲያ ሆሳዕና ከምሽቱ 12 ሰአት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።