ቀጥታ፡

የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል ዕድል ፈጥሮልናል- ተሳታፊ ድርጅቶች

አዲስ አበባ ሚያዝያ 23/2015(ኢዜአ):- የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ምርትና አገልግሎታቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር አብሮ የመስራት እድል እንደፈጠረላቸው የሁነቱ ተሳታፊ ድርጅቶች ገለጹ።


 

13ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ከሚያዚያ 19 እስከ 23/2015 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተካሄዷል።


 

በንግድ ትርዒቱ ላይ የተሳተፉ ድርጅቶች በመድረኩ ምርትና አገልግሎታቸውን ለማህበረሰቡ በማስተዋወቅ የተሳካ ስራ ማከናወናቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል ዕድል እንደፈጠረላቸው አመልክተዋል።


 

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኢንጂነር መላኩ አዘዘው፤ በመድረኩ ከ200 በላይ የውጭ እና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የተሳተፉበትና የተሳካ ውጤት የተገኘበት ነው ብለዋል።

ኩባንያዎች ምርታቸውን ያስተዋወቁበትና በትብብር ለመስራት ምቹ ሁኔታ የፈጠሩበት መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም