ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ ከጅቡቲ ወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀ-መንበር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 22/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ ከጅቡቲ ወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀ-መንበር አቡበከር ኦማር ሃዲ ጋር ተወያዩ።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።


 

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዛሬ ሚያዝያ 22/2015 ዓ.ም በዶራሌ ሁለገብ ወደብ፣ በጅቢቲ ነፃ የንግድ ቀጠና፣ በኤስ ጂ ቲዲ የኮንቴይነር ተርሚናል እና በድርጅቱ የጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጉብኝት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ከጅቡቲ ወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀ-መንበር አቡበከር ኦማር ሃዲ እና ከዶራሌ ሁለገብ ወደብ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃማ ኢብራሂም ዳራር ጋር መወያየታቸው ተጥቁሟል፡፡


 

ጉብኝቱ በቀጣይ ቀናትም በታጁራ ወደብ እና በዳመርጆ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እንደሚቀጥል ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች ለዋና ሥራ አስፈፃሚው የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም