ቀጥታ፡

የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን በወዳጅነት አደባባይ ሽኝት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ሚያዝያ 22/2015 (ኢዜአ)፦ የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን ሽኝት በወዳጅነት አደባባይ በመከናወን ላይ ይገኛል።


 

የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን በማርሽ ቡድን፣ በወዳጅ ዘመዶቻቸው እና በስራ ባልደረቦቻቸው ታጅቦ ወዳጅነት አደባባይ ከደረሰ በኋላ የሽኝት መርሃ ግብሩ እየተካሔደ ይገኛል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የአቶ ግርማ የሺጥላ የህይወት ታሪክ ቀርቧል።


 

በወዳጅነት አደባባይም የአቶ ግርማ የሺጥላ ባልደረቦች፣ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች አሸኛኘት እያደረጉ ሲሆን የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች የሃዘን መልዕክታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም በወላጆቻቸው ፍላጎት እና ጥያቄ መሰረት በተወለዱበት ሰሜን ሸዋ ዞን መሀል ሜዳ እንደሚፈጸም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም