የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20ኛውን ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20ኛውን ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ተረከበ
አዲስ አበባ ሚያዚያ 21/2015(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20ኛውን ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን መረከቡን አስታወቀ።
አውሮፕላኑ 30 በመቶ “Sustainable Aviation Fuel (SAF)” የተሰኘ የአውሮፕላን ነዳጅ የተጠቀመና ይህም በ2050 የካርበን ልቀትን ወደ ዜሮ ለማድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አቪዬሽን ኢንዱስትሪውን በሚመሩና በሚቆጣጠሩ አካላት የተያዘውን ውጥን ከግብ ለማድረስ እንደሚረዳ ገልጿል።
አየር መንገዱ የተረከበው አውሮፕላን 10 ቶን የሚመዝን ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ቁሳቁስም ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መምጣቱን አመልክቷል።