የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በማስመልከት የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ተካሄዷል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በማስመልከት የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ተካሄዷል
አዲስ አበባ ሚያዚያ 21/2015(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በማስመልከት የተዘጋጀ የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ዛሬ ተካሄዷል።
በውድድሩ ላይ ከሶስት ሺህ በላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
“ለኢንዱስትሪ እንሩጥ” በሚል በተካሄደው ውድድር ባለሃብቶች አትሌቶችና ሌሎችም ግለሰቦች መሳተፋቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአገር አቀፍ ደረጃ ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።